የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የማኔጅመንት አባላት ከኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስቴር እና ከዩኤንዲፒ ተወካዮች ጋር በመሆን፣ በኢትዮጵያ ጉብኝት ላይ ከሚገኘው የካንትሪ ፕላትፎርምስ ሃብ የልዑካን ቡድን ጋር ውይይት አካሂዷል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የማኔጅመንት አባላት ከኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስቴር እና ከዩኤንዲፒ ተወካዮች ጋር በመሆን፣ በኢትዮጵያ ጉብኝት ላይ ከሚገኘው የካንትሪ ፕላትፎርምስ ሃብ የልዑካን ቡድን ጋር  ውይይት አካሂዷል።

ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው ውይይት በኢትዮጵያ የተቀናጀ ዘላቂ የፋይናንስ ማዕቀፍ ተግባራዊ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ  የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ሚና በሚመለከት ውይይቱ ተካሂዷል፡፡

ውይይቱ  በዋናነት በሶስት አበይት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን የመጀመሪያው የባንኩ ስትራቴጂካዊ ሚና ሲሆን፣ ይህም አካታች፣ አረንጓዴ እና ዘላቂ ልማትን ለማስፋፋት እንደ ኢነርጂ፣ ውሃ፣ ግብርና፣ ትራንስፖርት እና ኢንዱስትሪ ባሉ ዋና ዋና ዘርፎች ላይ ያሉ የልማት ፋይናንስ ማስተሳሰርን ያጠቃልላል።

በተጨማሪም አዳዲስ የኢንቨስትመንት መንገዶችን ለመክፈት የባንኩን  ተልዕኮ እና የኢንቨስትመንት ይዘት ከንግድ ባንኮች፣ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና ከካፒታል ገበያዎች ጋር ማጣጣምን የሚመለከት መሆኑ ተገልጿል።

ሶስተኛው የውይይት ነጥብ በታቀዱ የቴክኒክ ድጋፎች ዙሪያ  ሲሆን ይህም ለባንኩ በአየር ንብረት ፋይናንስ፣ በአረንጓዴ ፕሮጀክቶች መዋቅር፣ እና የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ሀብቶችን በማቀናጀት ረገድ ወሳኝ የሆኑ የድጋፍ እና የአቅም ግንባታ ፍላጎቶችን መለየት ላይ ያተኮረ መሆኑ ተብራርቷል።

ባንኩ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን፣ በአገሪቱ  ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የልማት አጀንዳዎች  ለማሳለጥ የሚያስችሉ አስተማማኝ፣ ለባንክ ብድር ብቁ የሆኑ እና የአየር ንብረትን የሚቋቋሙ ዕድሎችን የያዘ ሰፊ መደላድል በመገንባት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።