የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አመራሮች ብርኒሂጎ ኢንተግሬት ፖልተሪ ፋርምስ ኃ/የተ/የግ/ማህበርን ጎበኙ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አመራሮች ብርኒሂጎ ኢንተግሬት  ፖልተሪ ፋርምስ ኃ/የተ/የግ/ማህበርን ጎበኙ።
ብርኒሂጎ ኢንተግሬት ፖልተሪ ፋርምስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የአንድ ቀን ጫጩት፣ የመኖ ምርት እና ዶሮ ስጋን በማቀነባበር ለዉጭ እና ለሀገር ዉስጥ ገበያ ለማቅረብ እ.ኤ.አ በ2014 የተቋቋመ ሀገር በቀል ድርጅት ነዉ።
ድርጅቱ በትግበራ ወቅት የገጠሙትን ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ማለትም የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣  የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና የሰላም ችግሮች ቢገጥሙትም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ችግሮችን በመረዳት እና አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ በአሁኑ ሰዓት ትግበራውን እንዲያጠናቅቅና የማምረት አቅሙን ከአንድ ቀን ጫጩት እና መኖ ማምረት ወደ የዶሮ ስጋን ማቀነባበር በማሳደግ በቀጣይ ወራት ጥራቱን የጠበቀ የዶሮ ስጋ በተመጣጣኝ ዋጋ ለሀገር ውስጥና ለዉጭ ገበያ ለማቅረብ መዘጋጀቱን በጉብኝቱ ወቅት አሳዉቋል።
2000 የሚደርሱ በዋናነት ሴት አርሶ አደሮችን በኮንትራት ፋርሚንግ አደራጅቶ እየተንቀሳቀሰ ያለዉ ድርጅቱ በመንግስት የተነደፈውን የልማት አቅጣጫ (የሌማት ትሩፋት) ጉልህ ሚናን ለመጫወት ይረዳዉ ዘንድ በአካባቢው ከ110 በላይ ለሆኑ ሰዎች ቀጥተኛ የስራ እድል ፈጠራ አበርክቷል። 
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአዋሽ ሰባት የሚገኘዉ ይህ ፋርም በባንኩ ልዩ ትኩረት ተሰቶት ወደ ምርት እንዲገባ የድጋፍ እና ክትትል ስራዎች መሰራታቸዉን አንዲሁም በተቋሙ የተለያዩ ተጨማሪ የኢንቨስትመንት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የባንኩ የስራ ሀላፊዎች ተዘዋዉረዉ በጎበኙበት ወቅት ለመረዳት ተችሏል፡፡
በተጨማሪ  በከባቢና አየር ጥበቃ እንዲሁም የራሱን የመኖ ግብዓት ለማሟላት ከ1000 ሄክታር በላይ  የእርሻ መሬት ከክልሉ መስተዳድር በሚደረግለት ልዩ ድጋፍ በመረከብ የመኖ ግብዓቶችን ከራሱ ከእርሻው ለመሸፈን ተጨማሪ የማስፋፊያ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።