የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዓለም አቀፉን የልማት (ፖሊሲ) ባንኮች ጥምረት – ፋይናንስ ኢን ኮመን (FiCS) ተቀላቀለ
- March 25, 2026
- Posted by: admin
- Category: News
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
ሚዲያና ኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክቶሬት
የፕሬስ መግለጫ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2018 ዓ.ም (March 25, 2026)
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዓለም አቀፉን የልማት (ፖሊሲ) ባንኮች ጥምረት – ፋይናንስ ኢን ኮመን (FiCS) ተቀላቀለ — የአፍሪካ ልማት ሻምፒዮን በዓለም አቀፍ የቀጣይነት ፋይናንስ መድረክ ላይ እመርታ አሳየ፡፡
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ — የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዓለም ታላቅ የመንግስታዊ የልማት ባንኮች (PDBs) ጥምረት የሆነውን Finance in Common System (FiCS) በይፋ መቀላቀሉን በታላቅ ክብር ያስታውቃል።
የFiCS ዋና ጸሐፊ አዳማ ማሪኮ በFiCS ማኅበረሰብ ስም የጻፉት በይፋ መቀበላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ይህን ወሳኝ እርምጃ ያረጋግጣል፤ ይህም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍታ የሚታወቅ የልማት ፋይናንስ ተቋም ሆኖ የሚታይበት ወሳኝ ጅማሬ ነው፡፡
ስለ ዓለም አቀፍ የልማት ባንኮች ጥምረት– FiCS
ዓለም አቀፍ የልማት ባንኮች ኅብረት በ2020 በፓሪስ ላይ የተካሄደው የመጀመሪያው የመንግስታዊ የልማት ባንኮችን ያቀፈ ጉባኤ ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላም ወደ ዓለም አቀፍ ታላቅ የልማት ፋይናንስ ተቋማት ጥምረትነት አድጎ ተስፋፍቷል። አሁን ከ530 በላይ የፖሊሲ(ልማት) ባንኮችን በአንድ ላይ ያካትታል፤ እነዚህም በአጠቃላይ 23 ትሪሊዮን ዶላር የሚጠጋ ንብረት ያስተዳድራሉ፤ በየዓመቱም ከ2.5 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት ያካሂዳሉ፤ ይህም ከዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ፍሰቶች ከ10% በላይ ነው።
ጥምረቱ ለመንግስታዊ የልማት ባንኮች የሚሆን ዓለም አቀፍ መድረክ ሲሆን፣ የእነሱን የስትራቴጂ አቅጣጫ፣ የኢንቨስትመንት ስምረት እና የአሠራር መንገዶች ከተባበሩት መንግስታት የቀጣይነት ልማት ግቦች (SDGs) እና ከፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነት ጋር አጣጥሞ ይሠራል። የጥምረቱ አባል ባንኮች በንቃት እየተሠራባቸው ያሉ ከአየር ንብረት ፋይናንስ እስከ ከተሞች ችግር የመቋቋም አቅም ግንባታ ዘርፎች ድረስ የ14 ያህል የተለያዩ ተጨባጭ የተግባር ማእቀፎችን የተመለከቱ የተሸሉ ተሞክሮዎችንና ልምዶችን ያጋራሉ፡፡ የጋራ ፋይናንስ ልማት ያካሂዳሉ እንዲሁም የዓለም አቀፍ የልማት ፋይናንስ አጀንዳን መልክ ያስይዛሉ ወይም ያቀናጃሉ።
የፋይናንስ ኢን ኮመን (FiCS) ሴክሬታሪያት ይህንን የአባልነት ሂደት የተቀላጠፈ ለማድረግ ትልቅ ሚና በተጫወተው የፈረንሳይ ልማት ተቋም – Agence Française de Développement (AFD) ተስተናግዷል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጥምረቱን የመቀላቀሉ አንድምታዎች፤
- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዓለም አቀፍ የፖሊሲ ባንኮች ጥምረት አባልነቱ የሚከተሉትን እድሎች እንደሚያገኝ ይታመናል፡፡
- ከ530 በላይ ዓለም አቀፍ የልማት ባንኮች የተሰበሰበና የተቀመረ እውቀት፣ ልምድና ተሞክሮ ለማግኘት ያስችለዋል፤
- በየአየር ንብረት ለውጥ፣ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች(SME) ፋይናንስ እና የፋይናንስ አካታችነት ላይ በትብብር መሥራት ያስችለዋል፡፡
- በጥምረቱ በፋይናንስ ዘርፍ አዳዲስ ሐሳብ ማመንጫ ማእክል (Innovation Lab) እና የመንግሥታዊ ልማት ባንክ (PDB) ዋስትና ማዕከል ውስጥ የተለያዩ ዕድሎች ይኖሩታል፡፡
- ተቋማዊ ታማኝነት እና ዝናውን ማሳደግ ያስችለዋል፡፡
- በባለ ብዙ የትብብር መድረክ አማካኝነት አካታችና ጥብቅ ባልሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች የሚሰጡ ፋይናንሶች የማግኘት ዕድሉን ያሰፋል፡፡
- ከዓለም ባንክ እና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር የጋራ የልማት ፋይናንስ አተገባበር እድሎቹን ያሰፋል፡፡
“የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፋይናንስ ኢን ኮመን (FiCS) በመቀላቀሉ በዓለማችን ውስጥ ካሉ የተለያዩ መንግስታዊ የልማት ባንኮች የተቀመረ ተሞክሮ፣ ልምድ እና እውቀትን በቀላሉ ማግኘት ያስችለዋል፡፡ እንዲሁም በስትራቴጂ፣ በኢንቨስትመንት እና በአሠራር ዘዴዎች ላይ የእውቀት ልውውጥም ይኖራል። በሚመጡት ወራትና ዓመታት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር የሚኖረንን አመርቂ ትብብር በጉጉት እንጠብቃለን።”— አዳማ ማሪኮ፣ ዋና ጸሐፊ፣ Finance in Common
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የዓለም አቀፍ የፖሊሲ ባንኮች ጥምረት- FiCS የጋራ የስምምነት ሰነድ (Joint Declaration) ፈራሚዎች መካከል አንዱ ሆኗል፡፡ ይህም ሁሉም በመላው ዓለም የሚገኙ መንግሥታዊ ልማት ባንኮች ሁሉን አቀፍ ቀጣይነት ያለው የወደፊት አኗኗርን ለመገንባት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም የሚያስችሉ ሥራዎች ለመሥራት እና ባለብዙ መድረክ ትብብር በመላው የዓለም የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ ለማጠናከር የገቡትን የጋራ ቃል ኪዳን የሚወክል ሰነድ ነው፡፡
ልባዊ ምስጋና ለፈረንሳይ የልማት ተቋም (AFD)
የፈረንሳይ የልማት ተቋም (AFD) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በፋይናንስ ኢን ኮመን (FiCS) ውስጥ በአባልነት እንዲታቀፍ ላደረገለት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ባንኩ ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ የፋይናንስ ኢን ኮመን ሰክረትሪያት አስተናጋጅ ተቋም እንደመሆኑ፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር ለረጅም ጊዜ በአጋርነት የሰራ ተቋም እንደመሆኑ፣ የፈረንሳይ የልማት ተቋም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዛሬ የዚህን ታሪካዊ የአባልነት ደረጃ እንዲያገኝ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል፡፡ የልማት ባንኮች በዓላማ፣ በርዕይና ተግቶ በመሥራት ሲተባበሩ ሊያስመዘግቡ የሚችሏቸውን ስኬቶች በኢትዮጵያ ልማት ባንክና በፈረንሳይ የልማት ተቋም መካከል ያለው አጋርነት አመላካች ነው፡፡
ስለ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንጋፋ የፋይናንስ ተቋም ሲሆን፣ በኢንዱስትሪ፣ በግብርናና በሌሎች የኢኮኖሚ መስኮች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የልማት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ የሚያደርግ ኢትዮጵያዊ የፋይናንስ ተቋም ነው፡፡ ባንኩ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን በፋይናንስ በመደገፍ ቁልፍ ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ ዕድገት በፋይናንስ ይደግፋል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ወደ ልማት የምታደርገውን ጉዞ በማፋጠን የአየር ንብረት ተጽእኖን የሚቋቋም ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ደረጃ ይደግፋል፡፡
የሚዲያ ግንኙነት
የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
📧 communications@dbe.com.et
🌐 www.dbe.com.et
