የኢትዮጽያ ልማት ባንክ የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማውን አካሄደ
- February 4, 2025
- Posted by: admin
- Category: News
ባንኩ በመጀመሪያ ስድስት ወራት ከፍተኛ የተሰብሳቢ ብድር እንደነበረው ነው የተገለጸው።
ጥር 23 እና 24 ቀን 2017 ዓ.ም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ባካሄደው የግምገማ መድረክ ላይ የኢትዮጽያ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድና የማኔጅመንት አባላት: የዋና መስሪያ ቤት ዳይሬክተሮች: የዲቪዠን ኃላፊዎች፣ የዲስትሪክትና የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች በተገኙበት ተካሂዷል።
የኢትዮጽያ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ በግምገማ መርሃ ግብሩ ወቅት እንዳሉት በየደረጃው ያለው የባንኩ አመራርና ሰራተኛ የተሰጡ ብድሮችን ተከታትሎ ማስመለስ እና አዳዲስ የሚሰጡ ብድሮች ጊዜያቸውን ጠብቀውና ጤናማ ሆነው እንዲመለሱ ማድረግ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት።
የቦርድ ሰብሳቢው አክለውም ባንኩ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውጤታማ ለማድረግ አመራሩና ሰራተኛው ሌት ከቀን መስራት እንደሚገባ ነው የጠቆሙት።
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት አፈጻጸም ባንኩ አጠቃላይ በብድር መልቀቅ: በብድር መሰብሰብ እና ሌሎች የባንኩ ዋና ዋና ተግባራት ያስመዘገባቸውን መልካም ውጤቶች ማስቀጠል እንዲሁም የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ ወራት የባንኩ ማኔጅመንትና ሰራተኞች በከፍተኛ ርብርብ በመፈጸም የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግብ መስራት እንደሚገባ አቶ ተክለወልድ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰ በበኩላቸው ባንኩ ባለፉት ስድስት ወራት ያስመዘገባቸው መልካም ውጤቶች እንቅፋቶችን በመፍታትና አስቸጋሪ አሰራሮችን በመቅረፍ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም የላቀ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
አፈጻጸሞችን በልዩ ትኩረት በመለየት በየደረጃው ያለውን አመራርና ሰራተኛ በአሰራር በማገዝ መፍታት እንደሚገባም ዶ/ር እመቤት መለሰ ገልጸዋል።
በተለይ ተንከባለው የመጡና ባንኩን ለችግር የሚዳርጉ የአሰራር ግድፈቶችን በትኩረት መፍታት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የባንኩን የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ የስትራቴጂና ቸንጅ ማኔጅመንት ዳይሬክተር ዶ/ር ሽመልስ አርአያ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት 10.3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 11.3 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ ከእቅድ በላይ ማሳካት ተችሏል።
በእለቱ የተካሄደው የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ግምገማው ብቻ ሳይሆን የባንኩ ቀጣይ ጉዞ ላይ በመምከር አቅጣጫ ለማስቀመጥ የተደረገ መሆኑም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በመንግስት የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት በሚያስችለው ቁመና ላይ ለማድረስ የተለያዩ የአሰራር ማሻሻያዎችን ለይቶ በመስራት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰ አስታወቁ።
የባንኩ ማኔጅመንትና ሰራተኛም ባንኩ ሀገራዊ አበርክቶን በተሟላ መልኩ እንዲወጣ ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ፕሬዚዳንቷ ጠይቀዋል።
በተለይ ጠንካራ የስራ ባህልን በመገንባት፣የውስጥ አሰራሮችን መፈተሸና ለስራ አመቺ ማድረግ፣የተሻሻሉ ፖሊሲዎችን እና መመሪያዎችን ማዘጋጀት፣ ለባንክ ስራ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር፣በውስጥ ኦዲት የሚሰጡ ግኝቶችን ፈጥኖ ማስተካከል፣ራስን ለከፍተኛ ለውጥ ማዘጋጀት፣ጥራት ያለው የብድር ስርዓት መዘርጋት፣ባንኩ ለሀገራዊ ልማት የሚያበረክተውን ፋይዳ ተረድቶ በትጋት መስራት እንደሚገባ ነው ዶ/ር እመቤት የገለፁት።
ፕሬዚዳንቷ ይህን ያስታወቁት የባንኩ የስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በተገመገመበት ወቅት ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ በግማሽ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ በሰጡት ማጠቃለያ እንዳሉት ከዚህ በፊት የተሰጡ ብድሮችን ወደ ጤናማነት ማምጣትና አዲስ የሚሰጡ ብድሮች ደግሞ የተጠኑና ወቅታቸውን ጠብቀው ሊመለሱ በሚችሉ መልኩ ማድረግ ይገባል።
ሰብሳቢው አክለውም ባንኩ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ቢያልፍም በጥሩ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ባንኩ ከፊቱ የሚጠብቁትን ፈተኛዎች በብቃት ለመወጣት በላቀ ትጋት መስራት ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአብዛኛው የፋይናንስ መለኪያዎች ጥሩ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፣ ከ13.3 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ማሰራጨቱ፣ ከ11.3 ቢሊዮን ብር በላይ ከብድር ተመላሽ ማድረጉ፣ከ7.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ፣ በተለይም ከዲቢኢ ቦንድ የተሰበሰበ ሀብት 9.3 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን በአፈፃፀም ሪፖርት