‎‎

የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን በፋይናንስ፣ በቴክኒክና በምርት ጥራት መደገፍ ለዘርፉ እድገት በሚኖረው ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት ተካሄደ

‎የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን በፋይናንስ፣ በቴክኒክና በምርት ጥራት መደገፍ ለዘርፉ እድገት በሚኖረው ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት ተካሂዷል::

የውይይት መነሻ የሚሆን ጥናታዊ ፅሑፍ በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ የግሉ ዘርፍ ልማት አናሊስት በሆኑት በአቶ ብስራት ተሾመ ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክን በመወከል በውይይቱ ሀሳባቸውን ያቀረቡት የባንኩ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው በላይ ናቸው፡፡

እንደ አቶ ጌታቸው ገለጻ ባንኩ ከየትኞቹም የፋይናስ ተቋማት በተሻለ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልዩ ትኩረት ሰጦ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንንተርፕራይዞችን እንዲቋቋሙ፣ እንዲስፋፉና እንዲያድጉ በርካታ ስራዎች መሰራታቸው ተመላክቷል።

ኢንተርፕራይዞችን በፋይናንስ፣ በቴክኒክ እና በምርት ጥራት መደገፍ የማምረት አቅም አጠቃቀምን ለማሳደግ፣ ተኪ ምርትን በስፋት ለማምረት፣ ኤክስፖርትን ለማሳደግና የዘርፉን አጠቃላይ ሀገራዊ ድርሻ ከፍ ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል።

የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ዘርፍ መሰረቱ መስፋትና ተወዳዳሪ መሆን እንዲችል የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ በመድረኩ ግንዛቤ ተወስዷል።

የዘርፉን ልማት ማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ማምጣት፣ የልማት ኢንሼቲቮችና ልዩ ልዩ የድጋፍ ማዕቀፎችን ማቅረብ እንደሚገባም በፅሑፉ ተመላክቷል።

የባንኩ አመራሮችና ሰራተኞች ከውይይቱ በኋላ ኤክስፖውን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

690579562_3