የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ከፈረንሳይ ልማት ባንክ (AFD) አመራሮች ጋር ውይይት አካሄዱ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶ/ር ኢሳያስ ካሳ ከፈረንሳይ ልማት ባንክ (AFD) አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ/ም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ ባንኩ ከፈረንሳይ ልማት ባንክ (AFD) ጋር በአዲስ መልክ የሥራ ግንኙነት ለመፍጠርና ባንኩ በየትኞቹ ዘርፎች ላይ የብድር አቅርቦት እንዳለው ለመገንዘብ ውይይቱ ማስፈለጉ ተነሥቷል፡፡
የፈረንሳይ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ዘርፎች ለመረዳትና በቀጣይ በጋራ ቢሰራባቸው ውጤታማ የሚሆኑ ዘርፎችን ለይቶ ለማጥናት የሚያስችል ውይይት መደረጉ በመድረኩ ተነስቷል፡፡