የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ከቻይና ልማት ባንክ አመራሮች ጋር ውይይት አደረጉ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶክተር ኢሳያስ ካሳ ከቻይና ልማት ባንክ ልዑካን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ/ም በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው የውይይት መርሃ ግብር ሁለቱ ባንኮች ካሁን ቀደም በትብብር ይሰሩባቸው በነበሩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በቀጣይ ቀደሞ የነበረውን ትብብር ለማስቀጠልና በአዳዲስ ዘርፎች ላይም በጋራ ለመሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በውይይቱ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶክተር ኢሳያስ ካሳን ጨምሮ የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ በቻይና ልማት ባንክ በኩል የባንኩ የቺንግሃይ ቅርንጫፍ የዓለም አቀፍ ትብብር ዲቪዥን ምክትል ዳይሬክተር ዱ ዴሁ (Du Dehu) እና ሌሎች የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
