የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የፖላንድ አምባሳደር ጋር ተወያዩ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢሳያስ ካሳ በኢትዮጵያ የፖላንድ አምባሳደር ሎና ኮርቹት Ilona Korchut ጋር በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡ሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው ውይይት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና የፖላንድ ልማት ባንክ (Bank Gospodarstwa Krajowego) በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ነጥቦች ዙሪያ ነው ውይይቱ የተደረገው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም የፖላንድ ካምፓኒዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት የሚያደርጉበትንና በባንኩ በኩል ስለሚደረግላቸው ድጋፍ መክረዋል፡፡