የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና የቤልጅየም- ሉክሰምበርግ የኢንዱስትሪ ና ግብርና ንግድ ምክር ቤት ውይይት አካሄዱ፡፡

ተቋማቱ በቤልጂየምና ሉክሰምበርግ የሚገኙ ትልልቅ ካምፓኒዎችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት እንዲሁም በተመሳሳይ ሁኔታ በኢትዮጵያ የሚገኙ ካምፓኒዎችን ወደ ቤልጂየምና ሉክሰምበርግ በመውሰድ የልምድ ልውውጥና የሥራ ትስስር መፍጠር በሚቻልባቸው ጉዳዮች እና በዚህ ሂደት ውስጥ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሚና ምን መሆን አለበት በሚሉና በጋር መሥራት በሚችሉባቸው ነጥቦች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ወ/ሮ አይዳ እርቅይሁን የሆልሴል ፋይናንሲንግ እና የውጪ ፈንድ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ አቶ ዮሃንስ ጥላሁን ሲኒየር ፕሬዝዳንት አማካሪ እና አቶ ሲራክ ሰለሞን ሲኒየር ቦንድ አማካሪ እንዲሁም የቤልጅየም- ሉክሰምበርግ የኢንዱስትሪእና ግብርና ንግድ ምክር ቤት ኮሜርሺያል ዳይሬክተር ሚስተር ቶማስ ዴ ቡሌ ተገኝተዋል፡፡