የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር ጋር ተወያዩ፤
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢሳያስ ካሳ በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር አሌሃንድሮ ኢስቲቪል (Alejandro Estivill) ጋር በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡
ሚያዚያ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው ውይይት በካርቦን ፋይናንሲንግ እና በካርቦን ቦንድ ላይ ባንኩ ለሚሠራቸው ሥራዎች የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርጉም አምባሳደር አሌሃንድሮ ኢስቲቪል ገልጸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም ከሜክሲኮ የሚመጡ የካርቦን ኤክስፐርቶች ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለሙያዎች ልምዳቸውን እንደሚያካፍሉ የተገለጸ ሲሆን በጋራ መሥራት በሚችሉባቸው ሌሎች ጉዳዮችም መክረዋል፡፡
