የኢንዱትሪና የግብርና መካናይዜሽን ግብአቶች አቅርቦትን የሚያግዝ ማኅበር ተመሠረተ።

በካፒታል እቃዎች ፋይናንስ አቅርቦት ና ውጤቶች እንዲመዘገቡ የሚቀርብ ብድር እያደገ መሆኑም ተገልጿል። የኢንዱትሪና የግብርና መካናይዜሽን ግብአቶች አቅርቦትን የሚያግዝ ማኅበር መመሥረቱን ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በተዘጋጀ ይፋ ማድረጊያ መርሃ ግብር ላይ ተገለጸ፡፡ የኢንዱሰትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መላኩ አለበል በተገኙበት በተዘጋጀው በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ከኢንዱስትሪ ሚንስቴር፣ የገንዘብ ሚንስቴር፣ የግብርና እና የሥራና ክህሎት ሚንስቴር፣ የብሔራዊ ባንክ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ተሳትፈዋል። በዚሁ መድረክ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ‹‹በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን የማምረቻ መሣሪያ አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ የማኅበሩ መቋቋም አስፈላጊ ነው›› ብለዋል፡፡