ኢትዮጵያ ልማት ባንክ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳትለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡
- August 24, 2024
- Posted by: admin
- Categories: News, Social Responsibility
No Comments
ኢትዮጵያ ልማት ባንክ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተጨማሪም የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ተጠሪ ተቋማት በጋራ የ10.7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በመገኘት አስረክበዋል፡፡ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳዳር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃይለ ሚካኤል የልማት ድርጅቶች ከመደበኛ ስራዎቻቸው ጎን ለጎን የማህበራዊ ኃላፊነት ተግባራቶቻቸውን በመወጣት ሰፊ ልምድ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ የልማት ድርጅቶቹ በአካል በመገኘት በዓይነት መደገፍና ተጎጅዎችን ማጽናናትን ጨምሮ በጥሬ ገንዘብም ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ኮሚሽኑ አደጋው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ የነፍስ አድን ስራ፣የስነ ልቦና ድጋፍና የመልሶ ማቋቋም ስራ እየሰራ መሆኑን በዚህም የተቋማት ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡