Grand Ethiopian Renaissance Dam Bond

is a bond which enjoys full government Guarantee. It is a bond marketed to finance the Grand Ethiopian Renaissance Dam which the government intends to build on Abay River.

Types of Bond Coupons and Their Characterstics Based on the actual situation in the country, the greate Ethiopian Renassance dam bond has the following characterstics

Bond Type

Prepared in the form of coupons: The minimum value of the bond is 50 birr, and in addition, they are offered with 20 different coupons

Payment Period

1-5 years and above 5 years: The interest rate for 1-5 year saving bonds is 7.5%. The interest rate for 6 years and above saving bond is 8%

Interest payement

Every year it will be on june 30 and Decemeber 31. Interest income from GERD bond is tax free

Benefits of GERD bond

It generates regular interest income for buyers/customers

The rate of interest paid on the bond is higher than the rate of the saving 

After 12 days after signing the bond, the buyer can sell it to another person or organization in the secondary market or transfer it by inheritance or gift 

Borrow money from the bank by keeping as guarantee

Do you want to buy GERD bond?

You can buy more than one saving bond of the couppon type you want , and the minimum purchase  is 50birr, An organization or individual who wants to buy the bond can register with the nearest ethiopian development bank or its agent and pay the approprate amount for the bond to be purchased .

ሕጻናት የቦንድ ግዥ መፈጸማቸውን ቀጥለዋል

በወ/ሮ አማካለች ከሊፋ አስተባባሪነት እና በወላጆቻቸው ድጋፍ ሕጻናት  በመጠናቀቅ ላይ ለሚገኘው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የቦንድ ግዥ በመፈጸም አስተዋጽዖ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡፡

ሕጻናቱ የቦንድ ግዥውን የፈጸሙት ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም በባንኩ ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት ነው፡፡

የባንኩ ተ/ም/ፕሬዚዳንት-ኮርፖሬት አገልግሎት አቶ ደሳለኝ ቦጋለ በዚህ ወቅት ግድቡ የሚሰራው ለነገ አገር ተረካቢ ለሆኑት የዛሬ ሕጻናት መሆኑን ገልጸው ድጋፉ በዚሁ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለወላጆች የአደራ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ጽ/ቤት አቶ መሰለ ብሩ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሁነቱን በማስተባበር ሕጻናቱን ለማበረታታት ያደረገውን አስተዋጽዖ አመስግነው፣ ሕጻናት በወላጆቻቸው መልካም እገዛ በዚህ የሀገራችንን የወደፊት እጣ ፈንታ በሚወስነው ታላቅ ፕሮጀክት ላይ በመሳተፋቸውም ደስ ሊላቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የሕጻናቱ አስተባባሪ ወ/ሮ አማከለች “ግድቡ የእኔ ነው!” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው የቦንድ ግዥ ዘመቻ ላይ ልጆቻቸውንና ጎረቤቶቻቸውን በማስተባበር የተካሄደ ቢሆንም የቦንድ ግዥው ሊፈጸም የቻለው ግን በልጆቹ በራስ ተነሳሽነት መሆኑን አብራርተው፤ ድጋፉም ከዚህ በተሻለ ለወደፊቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ሕጻናቱ በአጠቃላይ የብር 40 ሺህ የቦንድ ግዥ መፈጸማቸው ታውቋል፡፡

የ50ኛ ዓመት የጋብቻ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓልን ምክንያት በማድረግ የቦንድ ግዥ ተፈጸመ

ታዋቂው የፋይናንስ ባለሙያ አቶ ኢየሱስወርቅ ዛፉ እና ባለቤታቸው የ50ኛ ዓመት የጋብቻ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓላቸውን ምክንያት በማድረግ በባንኩ ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት ከወለድ ነጻ የሆነ የአንድ ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዥ ፈጽመዋል፡፡

በተያያዘም ኢንጂነር ተረፈ ራስወርቅ የዛሬ ስምንት ዓመት የ50ኛ ዓመት የጋብቻ የወርቅ ኢዮቤልዩን በማስመልከት በልጅ እና ልጅ ልጆቻቸው ሥም ለእያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር የቦንድ ግዥ ፈጽመው የነበሩ ሲሆን አሁንም በልጃቸው ሥም የብር 350 ሺህ የቦንድ ግዥ ፈጽመዋል፤ በአጠቃላይ ቤተሰቡ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግዥ አከናውነዋል፡፡

በቦንድ ግዥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ የህዳሴ ግድቡ ሙሌት ሥራ መጀመሩ ትልቅ ብሥራት መሆኑንና ለዚህም ባንኩ ከመጀመሪያው ጀምሮ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

 በተጨማሪም በቅርቡ ለግድቡ ግንባታ የብር 5 ሚሊዮን ቦንድ ገዝቶ በስጦታ መለገሱን፣ ከሥራ መሪዎች ጀምሮ ከደመወዛቸው ላይ እያዋጡ እንደሚገኙ እና የግድቡ ግንባታ ሥራ ስላልተጠናቀቀ ለወደፊቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል፡፡ በዚሁ ዓላማ አንጋፋዎቹ ሰዎች ባንኩ ድረስ በመምጣት የቦንድ ግዥውን በመፈጸማቸው ፕሬዚዳንቱ ከፍ ያለ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

አቶ ኢየሱስወርቅ ዛፉ የህዳሴ ጉዳይ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አስተዋጽዖ ያለበትና “አሻፈረኝ እምቢ የምትል ኢትዮጵያ ተፈጥራለች” በማለት የገለጹ ሲሆን ኢንጂነር ተረፈ ራስወርቅ በበኩላቸው “ግድቡ የእኛ ነው” የሚለው አባባል ትልቅ መልእክት ያዘለና ሁላችንንም የሚያስተሳስረን ነው ብለዋል፡፡