ስለ ኖቭል ኮሮና ቫይረስ /COVID 19/ ማወቅ የሚገባዎ ጥቂት ነጥቦች
በቻይናዋ ዉሃን ግዛት የተከሰው ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውጪ አገራችንን ጨምሮ ወደ በርካታ አገራት እየተዛመተ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ለግንዛቤዎ ይረዳዎ ዘንድ ስለ ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ምንነት እና እንዴት መጠንቀቅ እንደሚገባ የሚከተሉትን ሀሳቦች አስፍረናል፡፡
ኮሮና ቫይረስ ምንድነው?
የኮሮና ቫይረስ ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን ሞትን ሊያስከትል የሚችል ህመም ነው።
የቫይረሱ መተላለፊያ መንገዶች
በሽታው ያለበት ሰው ሲያስነጥስ፣ ባልበሰሉ ምግቦች፣ ከታማሚው ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ ይተላለፋሉ።
የበሽታው ምልክቶች
በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥ እና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል።
በሽታው የጠናባቸው ሰዎች ላይ ደግሞ እንደ የሳምባ ምች እና ከባድ የመተንፈሻ አካላት ህመም ይስተዋላል።
በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው ምልክቶች
- ቫይረሱ መጀመሪያ ጉሮሮን ያጠቃል፤ ስለዚህ ለ3 ወይም 4 ቀናት የሚቆይ የጎሮሮ ህመም ይኖራል፡፡
- ከፍተኛ ትኩሳት ያመጣል፡፡
- ከዚያም ቫይረሱ ከአፍንጫ ፈሳሽ ጋር ይዋሃድና አየርን ከአፍንጫ /ከአፍ/ ወደ ሳንባ የሚያመላልሰውን ቱቦ /trachea/ ያጠቃል፡፡ በመቀጠል ሳንባ ውስጥ ይገባና የሳንባ ምች /pneumonia/ ያስከትላል፡፡ ይህ ሂደት 5 ወይም 6 ቀናት ይወስዳል፡፡
- የሳንባ ምች ከፍተኛ ትኩሳት እና የመተንፈስ ችግር ያስከትላል፡፡
- በቫይረሱ ምክንያት የሚመጣውን የአፍንጫ መታፈን በጉንፋን ምክንያት ከሚያጋጥመው የተለመደ ዓይነት መታፈን ጋር ተመሳሳይ አይደለም፡፡ የመዘጋት፣ አየር የማጠር እና ራስን መቆጣጠር ያልቻሉ እንደሆነ ይሰማዎታል፡፡ በዚህ ጊዜ አፋጣኝ ትኩረት እና ክትትል ያስፈልግዎታል፡፡
- በበሽታው መያዝዎን ወይም ምልክቱ የታየባቸውን ሰዎች ሲያጋጥምዎ ሪፖርት ለማድረግ በነጻ የስልክ መስመር 8335 ወይም የመደበኛ ስልክ 0112-765340 መጠቀም ይችላሉ።
ስለ ቫይረሱ ተጨማሪ መረጃዎች
ይህ አዲስ በሽታ አምጪ ቫይረስ የጸሐይ ብርሃንን ጨምሮ ሙቀትን መቋቋም የሚችል አይደለም፤ በ26/27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በሆነ የሙቀት መጠን የሚሞት ነው፡፡
በቫይረሱ የተጠቃ አንድ ሰው ቢያስነጥስ፤ ቫይረሱ መሬት ሳያርፍ በአየር ላይ መንሳፈፍ እና መጓዝ የሚችለው ለ10 ጫማ ያህል ነው፡፡
ቫይረሱ በብረት ነገሮች ላይ ቢያንስ ለ12 ሰዓታት ያህል በህይወት መቆየት የሚችል ሲሆን ስርጭቱን ለመከላከል እና በቫይረሱ እንዳይጠቁ ማንኛውንም ብረት ነክ እቃ በነኩ ቁጥር ወዲያውኑ እጅን በንጽህና መጠበቂያ ኬሚካል (ሳሙና) በደንብ መታጠብ ያስፈልጋል፡፡ በጨርቅ ነክ (fabric) ላይ ከ6-12 ሰዓታት በህይወት ሊቆይ ይችላል ሆኖም የተለመደው የልብስ ማጠቢያ ሳሙና ይገድለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የሞቀ ውሃ መጠጣት ሁሉንም የቫይረስ ዓይነቶች ለማዳከም ውጤታማ ነው፡፡ ስለሆነም ፈሳሾችን ከበረዶ ጋር ሳይቀላቅሉ በብዛት መጠጣት ይመከራል፡፡
ኮሮና ቫይረስ በእጅ ላይ ከ5-10 ደቂቃ ብቻ በህይወት ሊቆይ ይችላል፡፡ ስለዚህ እጅን ደጋግሞ በሳሙና ማጠብ ያስፈልጋል፡፡ ከታጠቡ በኋላም ቢሆን እጅ ላይ ቫይረሱ ሊኖር ስለሚችል ዓይንን እና አፍንጫን መነካካት አያስፈልግም፡፡ ሞቅ ባለ ውሃ ትንሽ ጨው በመጨመር አፍን መጉመጥመጥ እና ከኢንፌክሽን ነጻ ማድረግ ይቻላል፡፡
በተጨማሪም ከሌሎች ሰዎች ጋር ንክኪ ማቆም ለምሳሌ አለመጨባበጥ፣ ሰዎች በብዛት በሚሰበሰቡበት እና መጨናነቅ ባለበት ቦታ አለመገኘት ይመከራል፡፡
በበሽታው መያዛቸውን የጠረጠሩ ሰዎች ምን ማድረግ አለባቸው?
ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ካለብዎ ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ይሂዱ።
የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አስራ አራት ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገራት ሄደው ከነበረም ይህንንም ለጤና ባለሙያ ያሳውቁ።
በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ጊዜ በሽታው ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ፣ በመሃረብ ወይም በሶፍት ይሸፍኑ።
አፍን አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃ እና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል።
በሽታው ወዳለባቸው ሃገራት ሲጓዙ ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች
ትኩሳት እና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ከፈጠሩ እጅን በሳሙናና ውሃ መታጠብ፣ ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋጽዖዎችን አለመመገብ፣ በሕይወት ካሉም ሆነ ከሞቱ የቤት እና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ፣ በተጨማሪም ስለ በሽታው በቂ መረጃ እንዲኖረዎ የሚመለከታቸውን አካላት ይጠይቁ፡፡
ተጨማሪ
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ በመጀመሪያ አንድ ጃፓናዊ አሁን ደግሞ 3 ጠጨማሪ ግለሰቦች /3 ጃፓኖችና 1 ኢትዮጵያዊ/ መያዛቸውንና እነርሱንም አስቀድሞ በተዘጋጀው የለይቶ ማከሚያ ተገቢው የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ፣ እንዲሁም ከበሽተኞቹ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦችም እንዲሁ ተለይተው አስፈላጊው ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የጤና ተቋማቱ መንግሥት የበሽታውን ሥርጭት ለመግታትና ለመቆጣጠር ተገቢውን እርምጃ እየወሰደ መሆኑን እንደሚያረጋግጡ በመግለጽ፣ ማኅበረሰቡ የመከላከያ መንገዶችን ችላ ሳይልና ሳይደናገጥ ተግባር ላይ በማዋል የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ምንጭ፡- ሪፖርትር ጋዜጣ፣ ፋና፣ ቢቢሲ አማርኛ እና ሌሎችም
ባንኩ ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ባንኩ አገራዊ ተልእኮውን በብቃት ለመወጣትና ኢኮኖሚውን ለመደገፍ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ፣ በዚህም የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ሪፎርም እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መግባቱን እና በስድስት ወሩ የሥራ አፈጻጸም ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በማብራሪያው ባንኩ በአዲስ አሠራር፣ አደረጃጀት እና የሪፎርም ጥናት ላይ መሠረት በማድረግ ወደ ሥራ በመግባቱ እ.ኤ.አ. 2018 ከተመዘገበው ኪሳራ ወጥቶ ትርፋማ መሆን መቻሉን የባንኩ ፕሬዚዳንት ገልጸዋል፡፡
የሪፎርም ዕቅዱ የተዘጋጀው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳን መሠረት በማድረግ፣ እንዲሁም የባንኩን ውስጣዊና ውጫዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን በማጣጣም መቀረጹን፣ በዕቅዱ ሰባት ምሶሶዎች መኖራቸውን፣ እነዚህ እንዲሳኩም “ባንኩ አለማቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ ልማት ባንክ” እንዲሆን ማስቻል የሆነ ራዕይ ቀርጾ እየሠራበት እንደሚገኝ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
በዚህም ባለፉት ሁለት ሩብ ዓመቶች (እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 01 እስከ ታህሳስ 31, 2019) ባንኩ ብር 6.27 ቢሊዮን ወይም የእቅዱን 83% ፈቅዷል፤ ብር 4.4 ቢሊዮን ደግሞ የለቀቀ ሲሆን 77% ከእቅዱ ለማሳክት ችሏል፤ እንዲሁ ብር 4.51 ሰብስቧል ይህም የእቅዱን 118% ፈጽሟል፡፡ ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በብድር መፍቀድ የ4% ጭማሪ፣ በብድር መልቀቅ የ7% ማነስ እና በብድር መሰብሰብ ደግሞ የ125% ብልጫ አሳይቷል ብለዋል፡፡
ባንኩ በተጠቀሰው ግማሽ ዓመት ከታክስ በፊት ብር 951.6 ሚሊዮን ትርፍ ሊያገኝ ችሏል፤ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ228% ብልጫ አለው፡፡ በመሆኑም አሁን ያለው የባንኩ ጠቅላላ ሀብትም ብር 89.4 ቢሊዮን መድረሱን አብራርተዋል።
ባንኩ ትርፋማ መሆን የቻለው በመላው ሠራተኛው ርብርብ፡ አዲሱ የባንኩ ሥራ አመራር ቦርድ ከሥራ አስፈጻሚው ጋር በጥምረትና በመተጋገዝ በመሥራቱ ሲሆን የተበላሸ ብድር መጠንን በመቀነስ እና አዳዲስ ፕሮጀክቶች ወደ ተበላሸ ብድር ጎራ እንዳይገቡ በመግታት ጭምር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመቀጠልም ከሚዲያ ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል፤ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል፡-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቢል /NBE Bill/፣ ብድር አቅርቦት እና አመላለስ፣ በአምስት ዓመቱ የስትራቴጂክ ሪፎርም እቅድ መጨረሻ የተበላሸ ብድር መጠንን በምን ያህል ለመቀነስ እንደታሰበ፣ ስለ አጠራጣሪ ብድሮች /NPLs/፣ በዝናብ ለሚለሙ እርሻዎች ብድር መቆሙ እና መቼ ለማስቀጠል እንደታሰበ፣ የውጭ ባለሃብቶች ከባንኩ ተበድረው ስለመጥፋታቸው እና ባንኩ ስለሚወስዳቸው እርምጃዎች፣ የፖሊሲው መሻሻል በልማቱ ላይ ያለው ፋይዳ እንዲሁም ከሊዝ ፋይናንሲንግን አገልግሎት ጋር በተያያዘ ናቸው፡፡
በምላሹም እስካሁን ድረስ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብር 52 ቢሊዮን ብድር መወሰዱን፣ እንዲሁም ባንኩ ጊዜውን ጠብቆ ብር 32 ቢሊዮን መመለሱን፣ ለባንኩ ቀጣይነት ለመንግስት የተጨማሪ ካፒታል ጥያቄ መቅረቡን ተናግረዋል፡፡
የአጠራጣሪ ብድር /NPL/ መጠን 34% እንደደረሰ የተገለጸ ሲሆን በስትራቴጂው ሪፎርም እቅድ መጨረሻም ወደ 10% በመቶ ለማውረድ እቅድ ተይዞ እየተሠራ እንደሚገኝ፣ አጠራጣሪ ብድር /NPL/ ማለት ሙሉ በሙሉ የወደመ ወይም የማይመለስ ማለት እንዳልሆነ ተብራርቷል፡፡ ብድራቸውን ባልመለሱ ተበዳሪዎች እና ተባባሪ በአጥፊዎችም ላይ አስተዳደራዊና እና ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ፣ የእርሻ ብድሮች ሙሉ በሙሉ አለመቆማቸው ለማሳያ ለቡና እርሻ፣ አበባ፣ ወተት ልማት ፕሮጀክቶች እና በመስኖ ለሚለሙ እንደሚሰጥ፣ ፕሮጀክቶቻቸውን ጥለው ስለጠፉ ባለሃብቶች ንብረቱን ተረክቦ በማስተዳደር ላይ እንደሚገኝ፤ ለምሳሌ አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ከ4500 በላይ ሠራተኞች እንዳይበተኑ የራሱን ማኅበራዊ ኃላፊነት እየተወጣ ቢገኝም ቀደምት ባለሃብቶቹ ያልተከፈለ ፍሬ ግብር፣ የሠራተኛ የጡረታ መዋጮ፣ የመብራት እና የተለያዩ እዳዎች ባንኩ አብሮ እንደተረከበ ተብራርቷል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፖሊሲው ማሻሻያ ብዙ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶችን የሚያበረታታ እንደሆነ፣ ከሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘም ባንኩ ወደዚህ ብድር ሲገባ በቂ ዝግጅት እንዳልነበረው ሆኖም ሥራው ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
DBE Carries Out 2nd Quarter Meeting
Development Bank of Ethiopia (DBE) had carried out its 2019/20 Second Quarter Management Members Meeting on January 31st and February 01, 2010 at the Ministry of Trade & Industry Conference Hall.
At the opening remarks, President of the Bank, Ato Haileyesus Bekele said that the objective of this meeting is to review and evaluate its performances against its plan and from the previous year same period.Accordingly, challenges over areas of improvement have been identified and discussed on the way forwards.
During the meeting, the 2019/20 Second Quarter Performance of the respective three selected districts namely Wolayita Sodo, Bahir Dar and Hawassa was presented. Similarly, the performance at the Bank level was also presented by vice presidents and Strategy, Change and Communication Directorate and profoundly evaluated and discussed by management members of the Bank.
Therefore, the Bank’s second quarter performance registers satisfactory labeling 87.7% by its BSC performance measurement an approving birr 4.09 billion (100%), disbursing birr 2.42 billion (74%) and collecting birr 1.21(81%) billion from project and lease financing services.
The strategic reform performance of the Bank also presented and discussed its progress comprehensively.
The Bank also sold Great Renaissance Dam Bond to birr 137.3 million during the quarter under review.
After the presentation, issues with respect to prudent lending, reducing NPLs, maximizing collection of loans and, increasing great renaissance dam bond sale especially by districts, establishing transparent system for promotion and transfer of employees and over all attitudinal change across employees and management members were openly discussed.
In conclusion, President of the Bank, Ato Haileyesus Bekele insists all management members of the Bank working at different levels encouraged to work aggressively in coming three months aims to meet the set targets for the budget year by increasing loan collection, reducing NPLs as well as achieving setback reform targets.
የቋሚ ኮሚቴ አባላት ከባንኩ ጋር ውይይት አካሄዱ፤ ጉብኝት አደረጉ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ5ወር የሥራ አፈጻጸም ዙሪያ ከከፍተኛ ሥራ መሪዎች ጋር ግምገማዊ ውይይት ታህሳስ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. አካሂደዋል፤ የመስክ ጉብኝትም አድርገዋል፡፡
ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ስለባንኩ የውስጥ አሠራር፣ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር፣ የሪፎርምና መልካም አስተዳደር ሁኔታ፣ የፕሮጀክት አስተዳደር እና ከዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ገለጻ ተደርጓል፡፡
በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ባንኩ ትርፍ ማስመዝገቡም ተብራርቷል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት ለእርሻ ሥራ ተበድረው ስላልሰሩ ባለሃብቶች፣ ስለተበላሽ ብድር፣ ህዝቡ ስለ ባንኩ ያለውን አመለካከት ለመቀየር የህዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈላጊነት እና በመሳሰሉት ዙሪያ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡
በምላሹም ለእርሻ ሥራ ብድር ወስደው ባልመለሱ ሃለሃብቶች እና የተበላሸ ብድርን በሚመለከት እጃቸው ያለበት ሰዎች ለህግ እየቀረቡ እንደሆነ፣ በባንኩ የተገዙ ኢንቨስትመንቶች እየተሰበሰቡ እንደሚገኝ፣ ለገጽታ ግንባታ ሥራ በአምስት ዓመቱ የባንኩ ስትራቴጂክ ሪፎርም እቅድ ውስጥ መካተቱ ተብራርቷል፡፡
በመቀጠል የቋሚ ኮሚቴው አባላት የባንኩ ፕሮጀክቶች በሆኑት አይካ አዲስ ጨርቃ ጨርቅ እና ቢ.ኤም.ቲ. ኬብል ማምረቻ ፋብሪካዎች ጉብኝት አካሂደዋል፡፡
በመጨረሻም በቀረበው ገለጻ እና በመስክ ጉብኝቱ አባላቱ ስለ ባንኩ የነበራቸው ግምት መቀየሩን እና የተሻለ ግንዛቤ ማግኘታቸውንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
Page 26 of 31