የጠባቧ ቤት ሰፊ በረከት
ብዙዎች የግል ሥራቸውን ለመጀመር እንቅፋት የሆነባቸው የቦታ እጦት እንደሆነ ሲናገሩ ይደመጣል፡፡ የመንቀሳቀሻ ገንዘብ አይቸግረኝም፤ ሆኖም የመሥሪያ ቦታ የለኝም የሚሉ ግለሰቦችን በተለያየ አጋጣሚ እንሰማለን፡፡ ወደምስራቅ ያገኘናቸው የቢዝነስ ሰው ‹‹የለም ለሥራ መሠረቱ ፍላጎትና
እና ቁርጠኝነት ነው እሱ ካለ መላ አለ›› ይላሉ፤ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት ሐረር ቅርንጫፍ ደንበኛ አቶ ሳሊ መሐመድ፡፡ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሊዝ ፋይናንስ የጥልፍ እና የስፌት ማሽኖችን ተረክበው እየሠሩ ነው፡፡ 35 ካሬ በሆነች ቦታቸው 24 ሰዓት በፈረቃ
ይሠራሉ ለነገ ስኬት ዛሬ ላይ የሚጣለው መሰረት ወሳኝ ነውና፡፡ አቶ ሳሊ ባላቸው ቦታ ላይ ትልቁን የቢዝነስ ትልማቸውን እስኪያሳኩ ድረስ ሌት ተቀን እየሠሩ መሠረታቸውን አስተማማኝ በሆነ ልምድና እና ካፒታል ላይ
እየገነቡ ይገኛል፡፡
በ1994 ዓ.ም ከቤተሰብ ጋር ወደ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ውስጥ የገቡት አቶ ሳሊ የቤተሰባቸውን ሥራ ጥለው በራሳቸው ሥራ የጀመሩት በ2000 ዓ.ም እንደነሆነ ይናገራሉ፡፡ የጨርቃ ጨርቅ ሥራን ከቤተሰብ
የወረሱት ሙያ ሲሆን፣ በእውቀት እና በፍላጎት እየሠሩት እንደሚገኙም አጫውተውናል፡፡ ሐረር ከተማ የስፌት ማዕከል ናት፡፡ አቶ ሳሊም የጨርቃጨርቅ ሥራቸውን
ለማስፋፋት ጥናት ጨርሰው ለኢንቨስትመንት የሚሆን ቦታ ተረክበው በግንባታ ሂደት ላይ ናቸው፡፡ ወደ ትልቁ የቢዝነስ ሥራቸው ከመግባታቸው በፊት ባላቸው ቦታ ላይ እዳቸውን እየከፈሉ፣ ሠራተኞቻቸውንም
ቤታቸውንም እየመሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አንድ ሰው ወደ ሥራ ከመሰማራቱ በፊት ለሥራው ያለውን ፍላጎት እና
በሚሰማራበት መስክ ላይ ያለውን እውቀት ማጤን እንዳለበትም ይመክራሉ፡፡
የአቶ ሳሊ 35 ካሬ የሥራ ቦታ ላይ 12 የድርጅቱ ሠራተኞች በፈረቃ ለ24 ሰዓት ይሠሩበታል፡፡ ግለሰቡ ቱርክ በነበራቸው የጉብኝት ቆይታ በጠባብ ቤት ተሠርተው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን መመልከታቸው በትንሽ ቦታ ላይ ምርታማ መሆን እንደሚቻል ልምድ እንደቀሰሙበት አልሸሸጉም፡፡ ኢንቨስትመንት የራሱ የሆነ ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ በተገኘው ቦታ ሥራን እየሠሩ ወደ ትልቅ የኢንቨስትመንት ሥራ መሸጋገር እንደሚቻል አቶ
ሳሊ ምስክር ናቸው፡፡ 24 ሰዓት እረፍት በሌላት ጠባቧ ክፍል በርካታ ጥልፍ፣ የሎጎ ሥራ፣ የፖለሲ አርማዎች ተሠርቷል፡፡ የ12 ሰው ደሞዝ የሚከፈል ገቢን ከመሸፈን ባሻገር፣ እዳ እየከፈለች የአቶ ሳሊን ቤተሰብ እያስተዳደረች ትገኛለች፡፡ ለዛም ነው አቶ ሳሊ ‹‹ይህቺ ቤት ታምረኛ
ናት›› የሚሉት፡፡ ለብዙ ሰዎች የሥራ እድል የሚፈጥር ፕሮጀክት ለመጀመር በሂደት ላይ ያሉት አቶ ሳሊ ህልማቸውን እንደሚያሳኩ ጅምር እንቅስቃሴያቸው ምስክር ነው፡፡ በአቶ ሳሊ ድርጅት የሚመረቱ ትራስ ጨርቆች ከ40 በመቶ በላይ ወደ ውጭ ነው የሚላኩት፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአቶ ሳሊ የስፌትና የጥልፍ ማሽኖች በሊዝ ፋይናንስ የብድር አገልግሎት አቅርቦላቸዋል፡፡ የባንኩ ባለሙያዎች በቅርብ እየተከታተሉ የሚደግፉ፤ የሚያነቁ መሆኑን
የሚናገሩት አቶ ሳሊ የባንክ የብድር ሂደትን በመሰልቸት የሚያፈገፍጉ ወደባንኩ ጠጋ ብለው የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ
ይመክራሉ፡፡ ትልልቅ ቢዝነሶች ገበያውን በመቋቋም ሳይናጉ ቀጣይ መሆን የሚችሉት መሠረታቸው ጠንካራ ሲሆን ነው፡፡ ሥራን በእውቀት እና በፍላጎት መምራት ውጤታማ ያደርጋል፡፡ አንድ ሥራ ለመሥራት ቦታ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ሆኖ ሳለ ባለ ውስን ካፒታል እና ቦታ ውጤታማ ሥራ መሥራት እንደሚቻል አቶ ሳሊን ጨምሮ የብዙ ግለሰቦች ታሪክ ያስተምረናል፡፡ ሁሉንም ነገር
በአንዴ ማሟላት የማይቻልበት ምክንያቶች ቢኖሩ ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ተደምረው የምንፈልገውን ውጤት ማምጣት ይቻላል፡፡ ቤታቸውንም እየመሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አንድ ሰው ወደ ሥራ ከመሰማራቱ በፊት ለሥራው ያለውን ፍላጎት እና በሚሰማራበት መስክ ላይ ያለውን እውቀት ማጤን እንዳለበትም ይመክራሉ፡፡