ባንኩ በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የገዛቸውን ተሸከርካሪዎች አስረከበ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት በማስጎብኘት የሥራ መስክ ለተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የገዛቸውን ተሸከርካሪዎች ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም. አስረከበ፡፡
በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የባንኩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንሲንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተሾመ አለማየሁ ባስተላለፉት መልዕክት የቱር ኢንዱስትሪ ምንም እንኳን የአገልግሎት ዘርፍ (Service) ቢሆንም በልዩ ሁኔታ የባንኩ አንዱ የትኩረት ዘርፍ ሆኖ አገልግሎቱ በመሰጠት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
አቶ ተሾመ አያይዘው ባንኩ ከዚህ ቀደም ለአስጎብኚ ድርጅቶች ላጸደቀው ሊዝ በተበጣጠሰ መልኩ ተሸከርካሪዎችን በአገር ውስጥ አቅራቢዎች በቀረበው መጠንና ጊዜ ለደንበኞቹ ሲያቀርብ እንደነበርና አሁን ግን የውጭ ምንዛሪ በማመቻቸት ከብር 42 ሚሊዮን 202 ሺህ በላይ በማውጣት ለ16 የሊዝ ደንበኞች 36 ለማስጎብኘት ሥራ የሚውሉ ተሸከርካሪዎችን የገዛ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 26 ተሸከርካሪዎችን ለ12 ደንበኞች በዚህ ዙር ርክክብ የፈጸመ ሲሆን ቀሪዎቹን 10 ተሸከርካሪዎች ደግሞ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚያስተላልፍ አክለው ገልጸዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተወካይ፣ ወ/ሮ ማሚት ይልማ በበኩላቸው ባንኩ ለቱሪዝም ዘርፍ መጎልበት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀው ተሽከርካሪዎቹ ለተቋቋሙበት ዓላማ እንዲውሉ አሳስበዋል፡፡
ተሽከርካሪዎቹ ተገዝተው ወደ አገር ውስጥ የገቡት በኢትዮጵያ ሞተርና ኤንጅነሪንግ ኩባንያ /ሞኤንኮ/ በኩል እንደሆነ ይታወቃል፡፡
DBE Carries Out 2nd Quarter Meeting
Second Quarter Management Members Meeting of the Development Bank of Ethiopia was carried out here in Addis Ababa at the Ministry of Trade & Industry Conference Hall on February 01-02, 2019.
During the meeting, 2018/19 Second Quarter Performance Report of the Bank at the corporate level was presented by the Strategy, Change and Communication Directorate as well as by the respective Vice Presidents and discussed comprehensively by management members of the Bank.
The Report covered the change related activities, credit operations, financial, HR and other function’s performance of the Bank for the second quarter and semi-annual, problems encountered, corrective measures taken, strengths and weaknesses observed and the way forward.
According to the Report, the credit operations performance of the Bank’s for this quarter is better than the previous year same period. Overall, the Bank registers satisfactory level performance by approving birr 3.94 billion, disbursing birr 2.39 billion and collecting birr 1.03 billion both in project and lease financing services.
The Bank also sold Grand Renaissance Bond amounted to birr 483.09 million during the quarter against its planned sales of 250 million.
Discussion is also held on the performance of the three selected districts, namely, Hawassa, Adama and Gondar and feedbacks were collected.
President of the Bank, Ato Haileyesus Bekele during his remark said the Bank is undergoing through transformation initiatives both in internal capacity and through external consultants and everyone in the Bank should cooperate for the successful implementation of these change initiatives and transforming the Bank. In addition, all management members need to be responsive by taking into account the risk that the Bank faces instead of being rigid for customer enquiries.
Finally, Ato Haileyesus insists all management members of the Bank working in different levels should work hard to contribute share to improve loan collection, reduce NPLs and minimize lengthy work process.
DBE Gets New Board Members
Some of the Newly Appointed Board Members
Development Bank of Ethiopia (DBE) has got seven new board members whom include Former Regional Director at UNDP, Tegegnework Gettu (PhD); Minister of Agriculture, Oumer Hussien; Former Minister of Agriculture, Tefera Derbew; Former Parliamentarian, Mesfin Nemera; Director of the State Think-Thank, Yohannes Ayalew (PhD); Esays Kassa and Mele’ekt Sahlu (W/rt).
Tegegnework Gettu (PhD) has appointed as Chairperson of the Board by replacing Shiferaw Shigute after receiving a letter of appointment.
The letter was issued on December 25, 2018 by Director General of Public Enterprises Holding and Administration Agency, Beyene Gebre Meskel.
Sileshi Lemma, Wondu Legesse, Tewodros Gebre-egziabher, Desalegn Ambaw, Zekarias Erkelo and Yitbarek Takele (PhD) were former board members of the Bank.
የፓናል ውይይት ተካሄደ
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ15ኛ እንዲሁም በሀገራችን ለ14ኛ ጊዜ የተከበረውን ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እስከ ቡድን መሪዎች ድረስ የተሳተፉበት የፓናል ውይይት ታህሳስ 05/2011 ዓ.ም. በንግድ ሚኒስቴር አዳራሽ ተካሂዷል፡፡
በዕለቱ “ሙስና የምድራችን ነቀርሳ” የሚል ቪዲዮ እና “ሙስናና ሥነ ምግባር የዘመኑ ቁልፍ ጉዳዮች” በሚል ርዕስ የባንኩ የሥነ ምግባርና ቅሬታ ማስተናገጃ ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ወርቁ ፈቃደ ለፓናል ውይይት መነሻ የሚሆን ጽሑፍ አቅርበው በተሳታፊዎች ዘንድ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
የሙስና አስከፊነት፣ በግብረ ገብነት መኖር የደስታ ምንጭ መሆኑ፣ ሞራል የመኖር እና ያለመኖር የመጨረሻ ጉዳይ መሆኑ፣ ሙስና ቤተሰብን ብሎም ሀገርን አጥፊ መሆኑ በውይይቱ ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ የተሰጠንን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ሙስናና ብልሹ አሰራርን መዋጋት እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን “ሁለንተናዊ ልማታችንን እና ሠላማችንን ለማረጋገጥ በሙስና ላይ እንዝመት፣ ጊዜው የተግባር ነው!!” በሚል በመሪ ቃል ተከብሮ ውሏል፡፡
Page 33 of 34